ኢትዮጵያ በ19ኛው የኮሜሳ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ በ19ኛው የኮሜሳ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች

AMN – ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በቡጁምቡራ-ቡሩንዲ እየተካሄደ በሚገኘዉ 19ኛው የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ (የኮሜሳ) የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች::

ጉባኤው “ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና፣ ማዕድንና ቱሪዝም ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በማጎልበት ክልላዊ ውህደትን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ኃላፊ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የተመራ ልዑክ ኢትዮጵያን ወክሎ በጉባኤው ላይ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል፡፡

ጉባኤው በኮሜሳ ቀጣና የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮች፣ በሽብርተኝነት፣የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review