ኢትዮጵያ ትምህርትን ለዜጎች በማቅረብ ረገድ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የተሻለ እድገት እንዳሳየች አንድ ጥናት አመላከተ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ትምህርትን ለዜጎች በማቅረብ ረገድ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የተሻለ እድገት እንዳሳየች አንድ ጥናት አመላከተ

AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ትምህርትን ለዜጎች በማቅረብ ረገድ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የተሻለ እድገት እንዳሳየች አንድ ጥናት አመላከተ

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ ከአፍሪካ የኢኮኖሚ ምርምር ኮንሰርቲየም ጋር በመተባበር “የሰው ሀብት ልማት በኢትዮጵያ” በሚል የፖሊሲ ውይይት እያካሄደ ነው።

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ፀጋ መድረኩ በኢትዮጵያ ያለውን የሰው ሃብት ልማት ለኢኮኖሚ እድገት ለመጠቀም ጠቃሚ ነው ብለዋል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ምርምር ኮንሰርቲየም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አቢ ከድር በበኩላቸው ሰዎች እንዲማሩና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ኢንቨስት ስናደርግ የምንፈልገውን የሰው ሃብት እናገኛለን ሲሉ ገልፀዋል።

ኮንሰርቲየሙ የሰው ሃብት ላይ በመረጃ የተመሠረተ ፖሊሲ ለማውጣት የሚጠቅም ምርምር እያደረገ ሲሆን የምርምሩን የመጀመሪያ ዙር ግኝት ለፖሊሲ አውጭዎች አቅርቧል።

ከተለያዩ ሚኒስቴሮች የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚህ ውይይት ጥናቱን ያቀረቡት በአፍሪካ የኢኮኖሚ ምርምር የምርምር ባለሙያ ካሪዛ ቴረንስ የኢትዮጵያ መንግስት የሰው ሃብት ላይ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ እያፈሰሰ ይገኛል ብለዋል።

ቴረንስ ኢትዮጵያ ትምህርትን ለዜጎች ለማቅረብ ረገድ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የተሻለ እምርታ እንዳሳየች ገልፀዋል።

በዚሁ ጥናት ጥራት ያለው የሰው ሃብትን ለማገኘት በቀዳማይ ልጅነት እና ቅደመ መደበኛ ትምህርት ላይ መስራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በጥናቱ ምክረ ሃሳብም መንግስት ጥራት ያለው የሰው ሀብት በማፍራት የሀገርን እድገት የተሻለ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

በመሀመድ ፈንታው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review