AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከስዊድን ፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አንደርሽ ሆል ጋር ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ እና ስዊድን ያላቸው ግንኙነት የረዥም ጊዜ መሆኑን አስታውሰው፤በፍትህ ዘርፍ እየተካሄደ ያለው ትብብርና የአቅም ግንባታ ድጋፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ሁለቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከውጭጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።