ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በግብርናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በግብርናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊዬቭ የተመራውን ልዑካን ቡድን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ሁለቱ ሀገራት በግብርና ልማት በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የግብርና ሁኔታ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ያብራሩ ሲሆን ግብርና ለኢትዮጵያ አጠቃላይ ዕድገት 1/3ኛ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ኤክስፖርት የግብርና ምርት መሆኑን ዶ/ር ግርማ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በእንስሳት ቁጥር በአፍሪካ ቀዳሚ ብትሆንም ከዘርፉ የሚደረገው ኤክስፖርት ዝቅተኛ መሆኑንና የግብርና ምርቶች ላይ እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ በመላክ ረገድም ብዙ መሰራት እንዳለበት ጠቅሰዋል።

ሁለቱ ሀገራት በእንስሳት እና በሰብል ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በውሃና መሬት አጠቃቀም፣ በዲጅታል ግብርና፣ በቴክኖሎጂ አተገባበር፣ በግብርና ምርቶች ግብይት፣ በመስኖና በሌሎች የግብርና ልማት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ምክክር ማድረጋቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review