ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በቴምር ልማት በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የከሊፋ ኢንተርናሽናል ቴምር አዋርድና የግብርና ኢኖቬሽን ዋና ፀሐፊ አብዱላሃብ ዘይድ(ዶ/ር) ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
የግብርና ሚኒስትር እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት የተቋቋመው የተባበሩት አረብ ኢሜሬት የከሊፋ ኢንተርናሽናል ቴምር አዋርድና የግብርና ኢኖቬሽን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል።
በፌስቲቫሉ የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎችና ቴክኖሎጂዎች፣ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል።
በአርሶ አደሮች፣ አምራቾችና አቀናባባሪዎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ቴምር አምራች አርሶ አደሮች፣ ባለሙያዎች፣ አምራቾች፣ የምርምር ዘርፉ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ነው የተባለው።
ኢትዮጵያ በግብርና ሚኒስቴር በኩል ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ፌስቲቫል ለማዘጋጀት ዝግጁ እንደሆነች ሚኒስትሩ መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
የአዋሽ ተፋሰስ እና ቆላማ አካባቢዎች አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ ከኦሮሚያ ክልል ደግሞ ጉጂና ቦረና ዞኖች ለቴምር ልማት ምቹ ሥነ-ምህዳር እንዳላቸውም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በቴምር ሊለማ የሚችል 500ሺህ ሄክታር መሬት ያላት ሲሆን እስከ አሁን የለማው ከስድስት ሺህ ሄክታር እንደማይበልጥና ሀገሪቱን ከምርቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።