የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ጋር በወንጀል ምርመራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽል በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ በዱባይ ወንጀል ሠርተው ኢትዮጵያ ውስጥ የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተከናወነ እነደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሌ/ኮለኔል አብደላ መሃመድ በበኩላቸው፣ በቀጣይ ለሚከናወኑ የጋራ የወንጀል ምርመራ ሥራዎች ወደ ዱባይ የሚሄዱትን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኃላፊዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት ተፈላጊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የወንጀል ምርመራ ቡድን በማቋቋም በትብብር እንደሚሠራ ሁለቱ ወገኖች መምከራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ የማህበራዊ የትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡