AMN-ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላን በጽ/ ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ አምባሳደሯን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ የፊንላንድ መንግስት በትምህርቱ መስክ በተለይም በልዩ ፍላጎት ትምህርት እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ሁለቱ አገራት በትምህርት መስክ የቆየ የሁለትዮሽ ትብብርና ወደጅነት እንዳላቸው የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታዋ ድጋፍና ትብብሩ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላችውን እምነት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸው፣ በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት መስክ ያለው ቆየ የሁለትዮሽ ትብብር እያደገ መምጣቱን ጠቁመው በቀጣይም ትብብርና ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።