AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም
ዛሬ ከተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቱኒዚያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ አሊ ናፍቲ ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት አሁን ላይ ያለውን የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ በማሳደግ በንግድ ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም ፣ ኢነርጂ፣አይሲቲ እና ትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መስኮች ዙሪያ መክረዋል።

የጋራ የሚነስትሮች ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ እና በአህጉሪቱ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ።
በተያያዘ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
ሚኒስትሮቹ ይሄንን ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ማድረግ እንደሚገባ መግባባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።