ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN-ኅዳር 21/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ብልጽግና ፓርቲም ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እንዲሁም እውነት፣ እውቀትና ጥበብን መለያው አድርጎ ባለፉት አምስት ዓመታት ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል ብለዋል።

በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችም የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ ናቸው። በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ አዳዲስ ድሎችን በማስመዝገብ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለመገንባት እንሰራለን ሲሉም አመልክተዋል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review