ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር ከ3.9 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር ከ3.9 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች

AMN – ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር የ30 ሚሊዮን ዩሮ (ወደ 3.96 ቢሊዮን ብር) የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የጀርመኑ ኬ ኤፍ ደብሊው የልማት ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር በርን ሎወን እና የባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ ፈርመውታል።

በሁለት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለመሥራት የተፈረመው ስምምነት፤ ሁለተኛው የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ የፈጠራ ሥራዎችን እና ሁለተኛው የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ ከፍ ለማድረግ ያለመ ድጋፍ መሆኑ ተመላክቷል።

በአሁኑ ጊዜ ግብርናን ለማዘመን እየተከናወነ ያለው በሁለተኛው ምዕራፍ የሚገኘው እንቅስቃሴም በሊዝ ፋይናንስ ላይ የተመሰረተ እንደነበር መገለፁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሀገራቱ መካከል የተደረሰው ስምምነትም ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉና ተስማሚ የሆኑ ኮምባይነሮችን እና ትራክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ማሽነሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያጋጥመውን የገንዘብ ችግር ለመፍታት ያለመ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review