AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ጋር ያላት የጸና ትብብርና የመሠረተ ልማት ትስስር ለጋራ ዕድገትና ለአዳዲስ ዕድሎች ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነውሲሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የኢትዮ-ሎጅስቲክስ የዘርፍ ማኅበራት በተዘጋጀው የቢዝነስ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ እየተካደ ነው፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ከጂቡቲ ጋር ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት አስፈላጊነት እና የኢትዮጵያ መንግስት በቀጣናው የንግድ እድሎችን ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ብለዋል።
ከጂቡቲ ጋር ያለን የጸና ትብብርና የመሠረተ ልማት ትስስር ለጋራ ዕድገትና ለአዳዲስ ዕድሎች ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነውም ብለዋል፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ተግዳሮቶችን በማስወገድ ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ስምምነት ጋር የሚስማማና አስተማማኝ የትብብር ማዕቀፍን እውን ለማድረግ በትጋት እየሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡
ማኑፋክቸሪንግና ግብርናን መሰረት ያደረገና ብዝሃነት ያለውን የውጭ ንግድ ለማስፋት እየሰራን ላለነው ስራ ጂቡቲ ስትራቴጂክ አጋራችን ነች ሲሉም አመልክተዋል፡፡