AMN – ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገው ሽግግር በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ድጋፎች እና የተገኙ ውጤቶች ሚናቸው የጎላ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ ከሌሎች የፌደራል የሱፐርቪዥን አባላት ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የጨርቃጨርቅ’የእንጨት ስራ እንዲሁም የቡና ኤክስፖርት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎቹ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ፍጹም በቀጣይ ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገው ሽግግር አመላካች ውጤቶች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
መንግስት ለእነዚህ ኢንዱስትሪዎች የበለጠ እንዲስፋፉ እና እንዲጠናከሩ ድጋፍ እና ክትት እንደሚያደርግም አመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱ የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
በአንዋር አህመድ