ኢትዮጵያ ከ100 አመት በላይ ያስቆጠረ የመከላከያ ተቋም ባለቤት መሆኗ የሚያኮራ ነው፡-ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ስላሴ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከ100 አመት በላይ ያስቆጠረ የመከላከያ ተቋም ባለቤት መሆኗ የሚያኮራ ነው፡-ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ስላሴ

AMN- ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከ100 አመት በላይ ያስቆጠረ የመከላከያ ተቋም ባለቤት መሆኗ የሚያኮራ እና የኢትዮጵያውያን የብርታት እና የጽናት ተምሳሌት ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ስላሴ ተናገሩ።

117ኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን “በፈተናዎች ውስጥ እየተገነባ የመጣ ሰራዊት” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

ኢትዮጵያ በመከላከያ ሰራዊት ጸንታ ቆይታለች ፤ቀጥላለችም ያሉት በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ስላሴ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያን ከየትኛውም አቅጣጫ ከሚቃጣ ጥቃት ለመመከት ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ በኋል በመከላከያ የተደረገው ሪፎርም ለሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት ጭምር ተምሳሌት የሆነ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

በበዓሉ ላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ክብርና ዝናን የሚያስተዋውቁ መርሃ ግብሮችን ሲያቀርቡ የነበሩ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች የመከላከያ የክብር አባልነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review