“ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ሃብት፣ የሰው ኃይል እና የመፈጸም አቅም አንጻር ፈጣን እድገት ታስመዘግባለች”:- ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

You are currently viewing “ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ሃብት፣ የሰው ኃይል እና የመፈጸም አቅም አንጻር ፈጣን እድገት ታስመዘግባለች”:- ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

“እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ተሟላ ብልጽግና” በሚል መሪ መልዕክት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪዎች እና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች መሪዎች ሥልጠና እየተሠጠ ነው።

በዚህ ሥልጠና ላይ የተገኙት የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በመጭዎቹ አራት አስርት ዓመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እመርታ እንደምታስመዘግብ ጠቁመዋል።

የትንበያ ጥናቱ ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ባሻገር የውጭ ሀገራት ባለሙያዎችም ያረጋገጡት ስለመኾኑ ነው የተናገሩት።

ሀገራት ባላቸው የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ ከሚያመርቱት ምርት እና ከሚጠቀሙት ቴክኖሎጅ አንፃር ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ተብለው በሦስት እንደሚከፈሉ አብራርተዋል።

ዶክተር ፍፁም ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ብትሰለፍም አሁን ላይ በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ካስመዘገቡ ሀገራት በ5ኛ ደረጃ፣ ከሰሃራ በታች ካሉት ሀገራት በ3ኛ እና ከምሥራቅ አፍሪካ ደግም ቀዳሚውን ደረጃ መያዟን አስገንዝበዋል።

በዓለም ባንክ በተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያ በ2021 እና በ2022 ዓ.ም በአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት 2ኛ ደረጃን እንደምትይዝ መጠቆሙን አብራርተዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ሃብት፣ የሰው ኀይል እና ይሄንን ማስፈፀም ከሚችል መንግሥት አኳያ ህልሟን እውን የማታደርግበት አንዳች ምክንያት እንደማይኖርም ማስረዳታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review