ኢትዮጵያ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከዩኔስኮ ተረከበች

AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም

በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ኢትዮጵያ በባህል ቅርስነት ያስመዘገበችውን የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራን ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከድርጅቱ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዳይሬክተር ላዛሬ ኤሎውዶ አሶሞ ተቀብላለች፡፡

ኢትዮጵያ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ስፍራን በባህል ቅርስነት ማስመዝገቧን በፓሪስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review