ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ

AMN- ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞስስ ቪላካቲ ጋር ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።

በምክክሩም በፈረንጆቹ መስከረም 2025 አጋማሽ ላይ ሊካሄድ ስለታሰበው የአህጉራዊ ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።

ዶክተር ጌዲዮን፣ ኢትዮጵያ ጉባዔውን በስኬት ለማስተናገድ ያላትን ተነሳሽነት እና ቁርጠኛነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ አፍሪካ ለአየር ንብረት ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠቷን እና ለስኬቱም ባለድርሻ አካላትን ከማሳተፍ አኳያ ጉባኤው ያለውን ጠቀሜታ አስረድተዋል።

ኮሚሽነር ሞስስ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ጉባዔውን ለማስተናገድ ያሳየችውን ፍላጎት እና ከወዲሁ እየተደረጉ ያሉትን የዝግጅት ስራዎች አድንቀዋል።

ኮሚሽነሩ አያይዘውም፣ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ቃል መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review