ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ዓለም አቀፍ ተፅእኖ ፈጣሪነቷን ከፍ ያደርገዋል፡ – አቶ ማሞ ምህረቱ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ዓለም አቀፍ ተፅእኖ ፈጣሪነቷን ከፍ ያደርገዋል፡ – አቶ ማሞ ምህረቱ

AMN – ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ዓለም አቀፍ ተፅእኖ ፈጣሪነቷን ከፍ ያደርገዋል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በ16ኛው የብሪክስ ጉባኤው ላይ ለመሳተፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ የልኡካን ቡድን ካዛን ሩሲያ ይገኛል።

አቶ ማሞ ምህረቱ ከሲጂቲኤን (CGTN) ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነትን መቀላቀሏ ከአባል አገራቱ ጋር ለሚኖራት የኢኮኖሚ ትብብር ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በካዛን ራሺያ እየተካሄደ የሚገኘው 16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ኢትዮጵያንና አዲዲስ አጋሮችን ሊጠቅሙ የሚችሉ የኢንቨስትመንት እና ዘርፈ ብዙ የትብብር እድሎች ላይ እንደሚመክር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት በማደግ ላይ ካሉ አባል አገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንድትፈጥር ምቹ ሁኔታን እንደሚይፈጥርላትም ተናግረዋል፡፡

የኢንቨስትመን ፍሰቱን እና የንግድ ልውውጥንም እንደሚያሳድገው አመልክተዋል፡፡

የብሪክስ አገራት ባለሃብቶች ባለብዙ የተፈጥሮ ጸጋ ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያ ጠቃሚ የኢንቨስትመን እና የንግድ ዕድሎች ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉም አቶ ማሞ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስረድተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review