የአፍሪካ የግምገማ ማህበር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከሰኔ 9 እስከ 11/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብራል።
የማህበሩን የምስረታ በዓል አስመልክቶ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ እና የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሚቼ ኦኢድራኦጎ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ ኢትዮጵያ ለግምገማ ስርዓት አስቻይ ሁኔታዎችን በመዘርጋት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።
በዚህም ተቋማዊ አቅምን በማጠናከር እንዲሁም የሰው ሃይልን በማብቃት አሰራር መዘርጋቷን ነው የተናገሩት።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሚቼ ኦውድራጎ በበዓሉ አከባበር ላይ በ25 ዓመታት የተሳኩ ውጤቶች፣ የሀገራትን አቅም ከማጠናከር አንጻር የተከናወኑ ተግባራት እና ቀጣይ ስራዎችን የተመለከቱ ዝግጅቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።የ
ማህበሩ የአፍሪካ ሀገራት በመረጃ ላይ የተመሰረተ የግምገማና የፖሊሲ ውሳኔ እንዲኖራቸው የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራት እንደገነቡት ተቋማዊ አቅም የተለያየ የግምገማ ስርዓት መኖሩን በማንሳት፥ ኢትዮጵያ የተሻለ የግምገማ ስርዓትና አቅም አላት ብለዋል።
በአፍሪካ የግምገማ ማህበር የምስረታ በዓል ላይ ከአፍሪካ እና ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ከ300 በላይ ተሳታፊዎች፣ የመንግስት ኃላፊዎች፣ ገምጋሚዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እንደሚገኙ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
ማህበሩ ፕሬዝዳንት ሚቼ ኦኢድራኦጎ በበዓሉ አከባበር ላይ በ25 ዓመታት የተሳኩ ውጤቶች፣ የሀገራትን አቅም ከማጠናከር አንጻር የተከናወኑ ተግባራት እና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ የተለያዩ ዝግጅቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።