ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማኅበራዊ ጥበቃን በገንዘብ ለመደገፍ ጥሩ ዕድል ፈጥሯል

You are currently viewing ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማኅበራዊ ጥበቃን በገንዘብ ለመደገፍ ጥሩ ዕድል ፈጥሯል

AMN – መስከረም 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማኅበራዊ ጥበቃን በገንዘብ ለመደገፍ ጥሩ ዕድል መፍጠሩን የዓለም ባንክ ተወካዮች ገለጹ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ተወካዮች ጋር በማህበራዊ ጥበቃ የፖሊሲ ማሻሻዎች፣ ቀጣይ ስለሚደረገው የማሕበራዊ ጥበቃ ኮንፍረንስና የከተማና የገጠር ሴፍቲኔት ፕሮግራሞችን በቅንጅት መደገፍ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት የዓለም ባንክ ለፖሊሲ ማሻሻያው እንዲሁም አጠቃላይ የማህበራዊ ጥበቃ ስራዎች ላይ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከመድረስና በቅንጅት ከመስራት አኳያ ክፍተቶች እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደስራዉ ባለቤት እስካሁን ከሌሎች ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን ከማህበራዊ ጥበቃ ምዝገባ ሂደት እስከ ፖሊሲ ማሻሻል ድረስ የተለያዩ ስራዎችን እያካሄደ እንደሚገኝ የገለጹት ሚኒስትሯ ለዚህም የዓለም ባንክ ትብብር ከመቼውም ጊዜ በላይ እስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዓለም ባንክ ተወካዮች በበኩላቸው አሁን ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የማኅበራዊ ጥበቃን ጨምሮ ሌሎች የልማትና የትብብር መስኮች ላይ በቅንጅት ለመስራት እንደሚያስችል ገልፀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ዘርፍ ለሚሰራው ስራ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review