AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በጋራ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ማህበራዊ ተሳትፎ ለማዋል ያለመ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የምጣኔ ሀብት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ተቋማቱ የሞባይል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ በተለይም በተለያዩ ሴክተሮች ምርታማነትን ለማሳደግ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከደንበኞች ጋር ለማስተሳሰር እና ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
እ.ኤ.አ.በ2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ የስራ እድሎች እንደሚፈጠሩ እና መንግስት ተጨማሪ 57 ቢሊዮን ብር ከታከሰ ገቢ እንደሚያገኝ በውይይቱ ተገልፃል።
እ.ኤ.አ. በ 2023 ዘርፉ 700 ቢሊዮን ብር ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አበርከቶ 57 ቢሊዮን ብር ከታክስ ገቢ አስገኝቷል።
የኢትዮጵያ ሃገር በቀል የኢኮኖሚ እድገት ፕሮግራም የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ማሻሻያ በዘርፉ ለሚስተዋለው እመርታ ትልቅ አስተዋጽዎ እያበረከተ መሆኑን Driving Digital Transformation of the Economy in Ethiopia በሪፖርቱ አመላክቷል።
በሪፖርቱ መሰረት የቴሌኮም ማሻሻያ እና የሞባይል ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንቶች በግብርና ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በህዝብ አገልግሎቶች በመሳሰሉት ቁልፍ ዘርፎች እድገትን እንዴት እንደሚያበረታቱ እመላክቷል።
በዚህ መነሻነት እ. ኤ. አ. በ2028 ከ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ስራዎች እንደሚፈጠሩ እና ለመንግስት ተጨማሪ 57 ቢሊዮን ብር ከታከሰ ገቢ ያስገኛሉ ተበሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በ 2028 ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ላይ ሊጨምር እንደሚችል ጂኤስኤምኤ በተባለ አለምአቀፍ ድርጅት በቀረበው አዲስ ሪፖርት ተመላክቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሩህ የሆነ የተሳሰረ የወደፊት ጉዞ ለማድረግ የጋራ ራዕይ መሰነቃቸውንም አመልክተዋል።
በአሸናፊ በላይ