ኢጋድ በቀጣናው የተፈናቀሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሁሉን አቀፍ ልማት ጋር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ አስገነዘበ

You are currently viewing ኢጋድ በቀጣናው የተፈናቀሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሁሉን አቀፍ ልማት ጋር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ አስገነዘበ

AMN – ግንቦት 14/2017 ዓ.ም

በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሁሉን አቀፍ ልማት ጋር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ገለጸ።

ኢጋድ በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለሚከሰቱ መፈናቀሎች እና በስደት ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የኢጋድ ምክትል ዋና ጸሀፊ መሀመድ አብዲ ዋሬ፣ በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ የሚፈናቀሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሁሉን አቀፍ ልማት እንቅስቃሴ ጋር ማስተሳሰር ያስፈልጋል ብለዋል።

በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለሚከሰቱ መፈናቀሎች መፍትሄ ለመስጠት የባለድርሻ አካላት ቅንጅት መጠናከር እንዳለበትም አመልክተዋል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ዘውዱ በዳዳ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከቀጣናው ሀገራት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመሆን ባህላዊ የካምፕ አቀራረብ ሞዴል ራዕይ መቅረጿን ተናግረዋል።

ይህም በቀጣይ ኢትዮጵያ የስደተኞችን እንክብካቤ ለማሳደግ ወደ ልማት ተኮር ስትራቴጂ ለመሸጋገር ያለመ አካታች ስትራቴጂ በቅርቡ እንደሚጀመር መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ረዳት ተወካይ ዴቪድ ካርፕ በበኩላቸው፣ በቀጣናው የሚደረገው የስደተኞች ምላሽ በለውጥ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ይህም አስደናቂ አመራር መኖሩን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review