ኤ ኤም ኤን ትውልድን ማነፅ ማስተማርና ማብቃት ላይ በትኩረት ይሰራል – አቶ ካሳሁን ጎንፋ
AMN – ሚያዝያ 09/2017
ኤ ኤም ኤን ለሚያስተምራቸው ህፃናት የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል መዋያ ድጋፍ አድርጓል።
የትውልድ ድምፅ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በልዩ ልዩ መስኮች በይዘት ረገድ ለህዝብ ተደራሽ ከመሆን ባለፈም፣ ትውልድን ማነፅ ማስተማርና ማብቃት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልጸዋል፡፡
ኤ ኤም ኤን በሰብዓዊ ተግባራትም ላይ የድርሻውን እያበረከተ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ተቋሙ ድጋፍ ለሚሹ 11 ህፃናት አስፈላጊ ክትትል በማድረግ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲማሩ እና የነገ ተስፋቸው ብሩህ እንዲሆን እያገዘ ይገኛልም ብለዋል።
ሆኖም ግን ይህ በቂ አይደለም ያሉት አቶ ካሳሁን፣ የእያንዳንዳችን ጥረት ሲደመር በርካቶችን ማገዝ የሚችል በመሆኑ በቀጣይም የተሻለ ስራ መሥራት እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡
አቶ ካሳሁን የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች ለሚያደርጉት ትብብር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ለህፃናቱ እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል ተመኝተዋል።
በማሬ ቃጦ