ኤ ኤም ኤን የከተማው ሕዝብ ድምፅ እንዲሆን እንፈልጋለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ኤ ኤም ኤን የከተማው ሕዝብ ድምፅ እንዲሆን እንፈልጋለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም

“የትውልድ ድምፅ” የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) የበለጠ የከተማው ሕዝብ ድምፅ እንዲሆን እንፈልጋለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 3ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽንን በተመለከተ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሆነው ኤ ኤም ኤን ጠንካራ የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ፣ ከተማ አስተዳደሩም ሚዲያው ሕዝቡን እንዲያገለግል እና የትውልድ ድምፅ እንዲሆን እያጠናከረው መሆኑን ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እና በግብዓት ተቋሙን የማብቃት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የጎደለውን እየሞላ እንዲያጠናክረውም ከንቲባዋ ጠይቀዋል።

ኤ ኤም ኤን የከተማው ሕዝብ ድምፅ መሆኑን በማንሣት ለዚህም ተገልጋይ እና አገልጋዩ ፊት ለፊት የሚገናኙበት “ዋርካ” እና ኅብረተሰቡ አስፈጻሚዎችን የሚጠይቅበት “አገልጋይ” ፕሮግራሞችን ለአብነት አንሥተዋል።

በፕሮግራሞቹ የሥራ ኃላፊዎች ከኅብረተሰቡ ለሚነሡ ጥያቄዎች መረጃ እና ማብራሪያ እንዲሰጡ እንደሚጠየቁ ነው ከንቲባዋ የገለጹት።

በመሆኑም የሕዝብ ቅሬታ የሚቀርቡባቸው ፕሮግራሞች የበለጠ እንዲጠናከሩ ሊበረታቱ ይገባል ብለዋል።

ኤ ኤም ኤን የሕዝቡን ችግር በተገቢው መንገድ በማቅረብ እና ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ለሚሠራው ሥራ ከተማ አስተዳደሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።

በሰፊና ሁሴን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review