እስራኤል እና ሀማስ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ

You are currently viewing እስራኤል እና ሀማስ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

እስራኤልና ሐማስ በጋዛ የተኩስ አቁም እና የታጋቾች የመልቀቂያ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ በኳታር ዋና አደራዳሪነት ለወራት ውይይት ከተደረገ በኋላ የተደረሰ ሲሆን ለ15 ወራት የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት መፍትሔ እንደሚያበጅለት ይጠበቃል።

እስካሁን በይፋ ያልታወጀው ስምምነት በመጀመሪያው ምዕራፍ የስድስት ሳምንታት የተኩስ አቁም ስምምነትን የያዘ ነው፡፡

በዚህም ስምምነቱ የእስራኤል ኃይሎች ከጋዛ ክልል እንዲወጡ እና ሃማስ ያገታቸው ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚያስችል መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

የስምምነቱ የመጀመርያው ምዕራፍ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶችን ፣ ሕፃናትንና ወንዶችን ጨምሮ 33 የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ ይጠይቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review