እንደ ሃገር የተመዘገበውን ውጤት የበለጠ ለማስቀጠል የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል-አቶ አለማየሁ እጅጉ

You are currently viewing እንደ ሃገር የተመዘገበውን ውጤት የበለጠ ለማስቀጠል የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል-አቶ አለማየሁ እጅጉ

AMN-ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

እንደ ሃገር የተመዘገበውን ውጤት የበለጠ ለማስቀጠል የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለከተማዋ የልዩ ወረዳ ፓርቲ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣ ስልጠናው ፓርቲው ከማእከል እስከ ወረዳ ባሉት መዋቅሮች አባላቱ በፓርቲዉ አጠቃላይ የአደረጃጀትና አሰራር ስርዓቶች፤ የፓርቲ ዲሲፕሊንና በኮሚሽኑ መመሪያዎች ላይ እውቀት በማዳበር የፓርቲና የመንግስት ተልዕኮዉን በሙሉ አቅም ለመወጣት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

እስከ አሁን በታየዉ የስራ ሂደት በኢንስፔክሽንና በስነ-ምግባር ፓርቲው በርካታ ለዉጦች ያስመዘገበ በመሆኑ እንደ ሃገር ከፍተኛ አፈፃፀም ማምጣቱን ጠቁመዋል።

ይህንን የበለጠ ለማስቀጠል የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን አቀናጅቶ ከመስራትና የፓርቲ አሰራርና ደንብ እንዳይጣስ አስጠብቆ ከመሄድ አኳያ ያሉትን ዉስንነቶች ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የከተማ ሴክተር ተቋማት ማስተባበሪያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብዱልሀዲ ረሻድ በበኩላቸው፣ የተቋም ግንባታ ላይ ያተኮረ እቅድ በማቀድ በዚህ ምእራፍ አባላትን እስከ ታች በማሰልጠን የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር በእዉቀት ለተልእኮ ዝግጁ ማድረግና ለዉጤት መብቃት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ተሳታፊ አባላትም ስልጠናዉ ወቅታዊና አቅምን የሚያጎለብት በመሆኑ የበለጠ ዉጤታማ ለመሆን በትጋት እና በቁርጠኝነት እንሰራለን ማለታቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review