እያጋጠመ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ መቋረጥ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ

You are currently viewing እያጋጠመ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ መቋረጥ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም ገለጸ

AMN-የካቲት 28/2017 ዓ.ም

ሰሞኑን እያጋጠመ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጥነት መቀነስ እና መቆራረጥ በቀይ ባህር ውስጥ በሚያልፍ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ መቋረጥ ምክንያት መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

በዚህም የተነሳ የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሌሎች አማራጭ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑን ኩባንያው ገልጿል፡፡

በመሆኑም አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ከአገልግሎት አቅራቢች ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ በመሆኑ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ይቅርታ መጠየቁን ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review