እድሜያቸው ለስራ ያልደረሰ ታዳጊ ህጻናትን ለቤት አጋዥነት ማሰማራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል- የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

You are currently viewing እድሜያቸው ለስራ ያልደረሰ ታዳጊ ህጻናትን ለቤት አጋዥነት ማሰማራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል- የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

AMN-ታህሣሥ 15/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከሆፕ ፎር ችልድረን ጋር በመተባበር በታዳጊ የቤት አጋዦች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር እያካሄደ ነው።

በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በመፍታት መብታቸው እንዲከበር እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን ተናግረዋል ።

ይሁን እንጂ እድሜያቸው ለስራ ያልደረሱ ታዳጊ ህጻናትን ለቤት አጋዥነት ማሰማራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

አካላዊ እና የስነልቦና ጥቃት እና ዘመናዊ የጉልበት ብዝበዛ በስፋት የሚደረስባቸው ጥቃት መሆኑም ተመላክቷል።ይህንን ችግር ለመፍታት የህግ ማዕቀፍ ለመዘርጋት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑም ተገልጿል ።

በዓለም ላይ ከ17 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ታዳጊ ህጻናት በቤት ሰራተኝነት ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል ።

በኢትዮጵያም በርካት ታዳጊ ህጻናት በቤት አጋዥነት ተሰማርተው እያገለገሉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በቀን በአማካኝ 9 ሰዓት እንዲሰሩ ይገደዳሉ ነው የተባለው።

እድሜያቸው ከ12 እስከ 17 የሚሆኑ ታዳጊዎችን ለቤት አጋዥነት የመቅጠሩ ሂደት በ37 በመቶ እየጨመረ መምጣቱ በመረጃው ተጠቁሟል።

በሩዝሊን መሀመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review