ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሮች ተመናምነው የነበሩ ደኖች እንዲመለሱ አድርገዋል፡- ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር)

You are currently viewing ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሮች ተመናምነው የነበሩ ደኖች እንዲመለሱ አድርገዋል፡- ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር)

AMN – ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም

ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሮች ተመናምነው የነበሩ ደኖች እንዲመለሱ ማድረጋቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራር እና ሠራተኞች በፈረንሳይ ጉራራ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።

ቢሮው ከየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ጋር በጋራ ባዘጋጀው መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሮች ተመናምነው የነበሩ ደኖች እንዲመለሱ አድርገዋል ብለዋል።

ሁሉም ማኅበረሰብ ባደረገው ርብርብ የከተማዋን የደን ሽፋን 17 በመቶ ማድረስ ስለመቻሉ ያነሱት ኃላፊው፣ እንደ ከተማ 20 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የከተማዋ ነዋሪ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በችግኝ ተከላ መር-ግብሩ የቢሮው አመራሮች እና ሠራተኞች፣ የየክፍለ ከተማ እና ወረዳ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ነዋሪች ተሳትፈዋል።

በትዕግሥት መንግሥቱ

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review