AMN- ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም
ከመላ ሀገሪቱ የተዉጣጡ የመገናኛ ብዙሀን አመራሮች እና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማቶችን እየጎበኙ ነዉ፡፡
የሚዲያ አመራሮቹ እና ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ ልማት አብዝተዉ ስለመደነቃቸዉ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የልማት ስራዉን እና የአዲስ አበባ የቱሪዝም ማዕከልነትን አጉልተዉ ለማሳየት ዝግጁ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ የተሰሩ የልማት ስራዎችን የመጎብኘት ሂደቱ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ፡፡
በተመስገን ይመር