ከመጪው ጥር ጀምሮ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ተግባራዊ ይደረጋል – የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

You are currently viewing ከመጪው ጥር ጀምሮ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ተግባራዊ ይደረጋል – የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

AMN – ጥቅምት 01/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከመጪው ጥር ጀምሮ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የ2017 ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ በሰጠት መግለጫ፣ በተቋሙ ላይ በተደጋጋሚ ሲነሱ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰዋል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን በአዲስ መልክ በማቋቋም እና የኢሚግሬሽን አዋጅን በማሻሻል በተሠሩ ሥራዎች በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ተጨባጭ ለውጦች እንዲታዩ ማድረጉንም ነው ያነሱት።

በ2017 በጀት ሩብ ዓመትም ተቋሙ የሰው ኃብቱን ለማሳደግ 125 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በማሰልጠን ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።

በሩብ ዓመቱ 478 ሺህ ቡክሌቶች ከውጭ መግባታቸውን እና ከዚህ ውስጥ 367 ሺህ ታትሞ ለደንበኞች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።

የኦንላይን የፓስፖርት ምዝገባ በቀን ከሰባት ሺህ በላይ መድረሱን እና የመዳረሻ እና ኦንላይን ቪዛ አገልግሎቶችም በተሻለ ሁኔታ እየተሰጡ እንደሆነ ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከመጪው ጥር ጀምሮ የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት እንደሚጀመር ገልጸው፤ ለዚህም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review