ከረሀብ ነጻ ዓለምን የመፍጠር ዓለም አቀፍ የጋራ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing ከረሀብ ነጻ ዓለምን የመፍጠር ዓለም አቀፍ የጋራ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም

ከረሀብ ነጻ ዓለምን የመፍጠር ዓለም አቀፍ የጋራ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ከጥቅምት 26 እስከ 28 ይካሄዳል፡፡

በምክክር መድረኩ ከ1 ሺ 500 በላይ የሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች፣ የግሉ ሴክተር፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የልማት አጋሮች፣ የሲቪክ ማህበራት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ አካዳሚዎችና ሚዲያዎች ይገኙበታል።

የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ መንግስት፣ በዩኒዶ (UNIDO)፣ በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) የቴክኒክ ድጋፍ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በምክክር መድረኩ የምግብ ዋስትናና የሚያረጋግጡ መርሀ ግብሮች፣ በግብርና፣ ተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪዎች እና ቱሪዝም ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎች፣ የኢንቨስትመንት ፎረም እና ከረሀብ ነጻ ዓለምን ለመፍጠር የሚያግዙ ውይይቶች እንደሚካሄዱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review