AMN – መስከረም 15/2017 ዓ.ም
የከተማዋ የስራ ሀላፊዎችና እና ከተለያዩ ቤተ እምነቶች የተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች የመስቀል ደመራ ስነ ስርዓት የሚከናወንበትን የመስቀል አደባባይ ስፍራን አፀዱ ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የፅዳት አምባሳደሮች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።
በዓሉ አብሮነትን በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር ለወራት ዝግጅት ስለመደረጉ ያነሱት የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዋና ፀሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በዛሬው የፅዳት መርሀግብር የሌሎች እምነት ተከታዮች መልካም ምኞታቸዉን ለመግለፅ መገኘታቸውን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስቅዱስ ይህ መርሀ ግብር የዘመናት የመቻቻልና የመደጋገፍ እሴትን ለማጠንከር ይረዳል ብለዋል።
ትእግስት መንግስቱ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!