ከተማዋን ፅዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የህዝብ የመልማት ፍላጎት የተረጋገጠበት ነው-ሙፈሪያት ካሚል

You are currently viewing ከተማዋን ፅዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የህዝብ የመልማት ፍላጎት የተረጋገጠበት ነው-ሙፈሪያት ካሚል

AMN-ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙና መጠነሰፊ የተቀናጁ የልማት ተግባራትን በትናንትናው ዕለት ተመልክተዋል።

ጉብኝቱን አስመልክተው የስራ እና ክህሎት ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸውቸ ባጋሩት መልዕክት፣ የአኗኗር ዘይቤን ያሻሻሉ፣ ፍትሐዊነትን የሚያረጋግጡ፣ አዳዲስ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማካሄድ ያስቻሉ፣ መነሻና መድረሻቸው ሰው ተኮር የሆኑ፣ ሰፋፊ የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት የተከናወኑ፣ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ድንቅና ስኬታማ ተግባራትን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ከተማዋን ፅዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የብልፅግና ዕሳቤዎች ወደ ተግባር የተቀየሩበት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ የአመራር ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት የታየበት የህዝብ የመልማት ፍላጎት የተረጋገጠበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ያሳዩትን ትጋት አድንቀዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review