ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው

AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

“ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በዓድዋ መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ “የዘመኑ አርበኝነት ለሰላም ዘብ መሆን እና ሌሎች ሰላም እንዲሆኑ መሥራትን ይጠይቃል” ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሀም ታደሰ በበኩላቸው፣ ሰላምን በማፅናት በኩል የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የሕዝብ የሰላም ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መርሐ-ግብሩ ላይ የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች እና አደ ሲንቄዎች፣ የሰላም አምባሳደሮች እና የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።

በትዕግሥት መንግሥቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review