ከታጠቁ ሐይሎች ጋር መንግስት ያደረገው ስምምነት ሕብረተሰቡ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመራ አስችሏል -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing ከታጠቁ ሐይሎች ጋር መንግስት ያደረገው ስምምነት ሕብረተሰቡ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመራ አስችሏል -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

AMN – ጥር 9/2017 ዓ.ም

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ተሃድሶ ስልጠና በማስገባት ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ሰላምና መረጋጋት በማስፈን ላይ መንግስት አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን በማንሳት በዚህም በየአካባቢዎቹ የሰዎች እና የሸቀጦች ዝውውር እየተካሄደ ነው ብለዋል የአገልግሎቱ ሚኒስትር።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው 30 በመቶ የነበረውን የዋጋ ግሽበት 17 በመቶ ዝቅ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

ይህ ማለት የሸቀጦች ዋጋ አልጨመረም ማለት አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ የሸቀጥ ዋጋ ዕድገት ማቆም አይቻልም ጤናማ እንዲሆን ማድረግ እንጂ ብለዋል።

ገቢን የማሳደግ እና ለገቢ ማሳደጊያ የሆነ ፕሮጀክቶችን መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋፋት ገቢን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን እና ወጪን መቀነስና መጋራት ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ባለፉት ወራት በርካታ ጉባኤዎችን ማስተናገዷን በመግለጽ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤንም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በሚያስገኝ መልኩ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

የጥምቀት በዓልን ለአብሮነት እና ለብሄራዊ ትርክት መጠቀም እንደሚገባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review