AMN- ሀምሌ 4/2016 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች በምስጋናው ወቅት እንዳሉት የኮሪደር ልማት ስራው የእያንዳንዱ ቀን እና ምሽት ስራ እየተገመገመ የሚስራ ስራ ነው፡፡
ልማቱ ለመረጠን እና ቃል ለገባንለት የከተማችን ነዋሪ የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ፤ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋት እና በማሳለጥ ለከተማችን የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለን ነዉ ብለዋል፡፡
በሂደቱም በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።
በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት እንዲሁ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ ሳይት በየምሽቱ በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ማለታቸውን ከአዲስ አባባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!