ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁለተኛው ዙር እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ገመገሙ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁለተኛው ዙር እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ገመገሙ

AMN- ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሁለተኛ ዙር በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ገምግመዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁለተኛው ዙር በተጀመሩት ስምንቱ የኮሪደር ልማት በሚከናወንባቸው አካባቢዎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎችም ዙሪያ ተወያይተዋል::

በውይይት መድረኩም ከንቲባ አዳነች በዕቅዳችን መሰረት ቅድሚያ የሚተገበሩ ተግባራትን በመለየት በጥራት፣ በፍጥነት እና እንደከዚህ ቀደም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ እና በመተግበር ከተማችንን ውብ፣ ፅዱ፣ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በትኩረት መስራት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበናል መለታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review