AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በከተማዋ የኮንፍራንስ፣ የቱሪዝም እና የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት የሚያረጋግጡ፣ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ እንዲሁም ለነዋሪዎች የስራ እድልን በሰፊው የሚፈጥሩ የአዲስ ኢንተርናሽናል የኤግዚቢሽንና የኮፍረንስ ማዕከል፣ ከዚያ ጋር ተያይዞ እየተሰራ ያለውን የለሚ ፓርክ፣ አየር መንገድ-ጎሮን ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ጋር የሚያገናኘዉ መንገድ ግባታ እና የአረንጏዴ ልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ በተገቢ ጥራት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን በፍጥነት ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ በቅርበት ክትትል እያደረግን በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል።