ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ሰጡ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ሰጡ

AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በከተማዋ ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 21 ነጥብ 4 በመቶው ማለፊያ ውጤት ያመጡ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እና የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፣ ዋን ፕላኔት እና የኔታ አካዳሚ ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ አሳልፈዋል።

በመርሀ ግበሩ ላይ ያለንበት ወቅት እድልም ተግዳሮትም ያለበት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ውጤታማ የሆኑት ተማሪዎች ተግዳሮትን አሸንፈው እና ያለውን መልካም እድል ተጠቅመው ስኬታማ የሆኑ ናቸው ብለዋል።

በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን እየተከናወነ ባለው ተግባር ከግዜ ወደ ግዜ በዘርፉ የሚገኘው ውጤት እየተሻሻለ መምጣቱን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች እንደ ከተማ የተመዘገበው ውጤት ለበለጠ ስኬት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደር ለትምህርት ዘርፉ የሰጠነው ትኩረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባ አዳነች በቀጣይ ግዜያት የበለጠ የላቀ ውጤትን እንጠብቃለን ሲሉም ተናግረዋል።

በትምህርት ዘርፉ እያደረግን ያለው ኢንቨስትመንት የሀገር ግንባታችን አካል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ተማሪዎች በቀጣይ የትምህርት ምዕራፍ በመልካም ስነምግባር በስኬታማነት እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review