ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአንበሳ ጋራዥ ጃክሮስ እና ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ለህዝብ አገልግሎት ክፍት መደረጉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአንበሳ ጋራዥ ጃክሮስ እና ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ለህዝብ አገልግሎት ክፍት መደረጉን ገለጹ

AMN ሰኔ 1/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በመሆን ከአንበሳ ጋራዥ ጃክሮስ እና የጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አድርገናቸዋል ብለዋል።

ይህ መስመር የትራፊክ ፍሰቱ መጨናነቅ የሚታይበት እና ለአደጋ የተጋለጠ ነበር አስቸጋሪ መስመር ነበር።

አሁን ደረጃውን የጠበቀ አስፖልት ፣ የእግርኛ መንገድ እና የብስክሌት መስመር ፣ የህፃናት መጫዎቻ ፤ የመኪና ፓርኪንግ ፣ታክሲ እና አዉቶቢስ መጫኛና ማዉረጃ ፣የህዝብ ማረፊያ ክፍት ቦታዎች፣የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች እና የንግድ ቤቶች ከመንገድ ዳር ያላቸው ርቀት ታሳቢ ተደርጎ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ አካታች መሰረተ ልማት ያካተቱ ናቸዉ።

ከጎሮ ዋና መስመር ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች እና ከቦሌ አለም አቀፍ የበረራ ጣቢያ በኩል የሚመጡ ተሸከርካሪዎችን በማስተንፈስ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ መፍትሔ ይሰጣል።

በተጨማሪም ሰፊ የንግድ የስራዎች እንዲፈጠሩ በማስቻል በሺዎች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ነዉ።

ሁሌም ህዝብን መሠረት ያደረገ ልማት መስራታችን ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ የምናስረክባት አዲስ አበባ ንፁህ ፣ ፅዱ፣ ውብ አበባ እና ለመኖር ምቹ ለጐብኝዎች ተመራጭ እስከምትሆን ሌት ተቀን መትጋታችንን አጠናክረና እንቀጥላለን።

በኮሪደር ልማቱ መስመር የተካተቱ ስራዎች ፦

4ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ ፤ ከ8 ኪሎ ሜትር በላይ ደረጀውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ ፤ 3 የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ቦታዎች ፣ የህፃናት መጫዎቻዎች ፣ 7 ፕላዛዎች ፣ 6 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ፣ ፋውንቴኖች 13 ታክሲ መጫኛና ማዉረጃ ፣ እና 872 ሱቆች ይገኙበታል ::

ዉድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን የልማት ስራ አጠናቀን እነሆ ስንላችሁ የናንተ መሆኑን በመረዳት እየጠበቃችሁት እንድትጠቀሙበት እያልኩ ለነበራችሁ ድጋፍ ፣ ላደረጋችሁት ትብብር እና ተሳትፎ ምስጋናዬን በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review