ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከያንጆ ከተማ የሲፒሲ ሴክሬተሪ ከሆኑት ሚስተር ዋንግ ጅንጂአን ጋር ተወያዩ

AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቻይና ጂያንግሱ በነበራቸው የሁለት ቀን ጉብኝት ከያንጆ ከተማ የሲፒሲ ሴክሬተሪ ከሆኑት ሚስተር ዋንግ ጅንጂአን ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ለይ በትብብር ለመስራት መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና ቴክኒክ ትብብር ጉዳዮች ሊቀ መንበር ሚስተር ሶንግ ቺንቦ ጋር ተገናኝተው በትብብር አቅጣጫዎች እና ዘርፎች ዙሪያ መወያየታቸውን እና በቀጣይ አብሮ ለመስራት መግባባታቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በናንጂን እና በያንጆ ከተሞች ባደረጉት ጉብኝት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ግብዓት የሚሆኑ ልምዶች መቅሰማቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ እና የከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክቶችን፤ የመኖሪያ ቤቶችን በስፋት ለመገንባት ከተማ አስተዳደሩ ለያዘዉ እቅድ ግብአት የሚሆኑ ፣ በፍጥነት እና በጥራት ለማከናወን የሚያስችሉ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም በጥራት እና ስፋት እየተተገበሩ ያሉትን የከተማ ግብርና ስራዎችን መጎብኘታቸውንም ከንቲባዋ አስታውቀዋል።

በጉብኝታቸው የተመለከቷቸውን እና ለኢትዮጵያ ተስማሚ የሆኑትን የግንባታ የቴክኖሎጂዎች እና የእውቀት ሽግግር ላይ ለመስራት መግባባታቸውንም ከንቲባዋ አውስተዋል፡፡

All reactions:

3636

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review