የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 10ኛው የሳይንስ እና የፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽንን በወዳጅነት አደባባይ አስጀምረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው ኤግዚቢሽኑ “በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ዛሬ የተጀመረው።
በመድረኩ የተለያዩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤቶች ከሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ተማሪዎች እና መምህራን ቀርቦ እየተጎበኘ ይገኛል።
የሳይንስ እና የፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽኑ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ክፍት እንደሚሆንም ተመላክቷል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ