AMN-ሰኔ 03/2016 ዓ.ም
ከአምስቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች የአንዱ መጠናቀቁ እና ለህዝብ አገልግሎት ክፍት መሆኑ ከታላላቅ ስኬቶች አንዱ እንደሚያደርገው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
ከአራት ኪሎ ራስ መኮንን ድልድይ፤ ከደጎል አደባባይ – ቀይባህር ኮንደሚኒየም እና ከማህሙድ ሙዚቃ ቤት- በቴዎድሮስ አደባባይ ያሉት መንገዶች ድንቅ በሆነ ደረጃ ተሰርተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ማራኪ ገጽታን እና የመገናኛ እንቅስቃሴን እንደሚፈጥሩ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን ትናንት ማምሻውን በለሙት ኮሪደሮች ጉብኝት ማካሄዳቸውም ተገልጿል።
የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ገምግመዋል፤ የውበትና አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን እና የዕድሳትም አድንቀዋል ብሏል ጽ/ቤቱ ።
ይህ ጉብኝት መንግሥት ለተሻሻለ የመንገድ ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ብሎም ለኑሮ ምቹ የሆነ ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባጋራው መረጃ አመልክቷል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!