AMN- ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም
በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ መታየቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፍያ በሰላም በማረፍ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ የቻለ ሲሆን አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ መሆኑንም አስታውቋል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል።