ከጃፓን አቶሚክ ቦምብ ጥቃት በሕይወት የተረፉ ሰዎች የ2024 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

You are currently viewing ከጃፓን አቶሚክ ቦምብ ጥቃት በሕይወት የተረፉ ሰዎች የ2024 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

AMN – ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

የ2024 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ከሰዓታት በፊት ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም በሁለተኛው ዓለም ጦርነት በጃፓን የሂሮሽማ እና ናጋሳኪ ከተሞች ከፈንዱት አቶሚክ ቦምቦች የተረፉት የጃፓናውያን ቡድን “ኒሁን ሂዳንኪዮ” የ2024 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በሂሮሺማና በናጋሳኪ ላይ ከደረሰው የቦምብ ድብደባ በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ያቀፈውና በ1956 የተቋቋመው ድርጅት ዓለምን ከኑክሌር የጦር መሣሪያዎች ለማስወገድ ባደረገው ጥረት በኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ እውቅና አግኝቷል።

ሰላምን በማምጣት እና ስለ ሰላም ለሰሩ ግለሰቦች አሊያም ተቋማት ለሚሰጠው የኖቤል የሰላም ሽልማት ዘንድሮ ከ286 በላይ ግለሰቦች እና ተቋማት በእጩነት ቀርበዋል።

ለዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት ከቀረቡት መካከል 197 ግለሰቦች ሲሆኑ፣ 89 ደግሞ ተቋማት መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

የኖቤል ኮሚቴ ስድስት ሽልማቶችን የሚሰጥ ሲሆን እነዚህም የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ሥነ-ልቦና ወይም ሕክምና፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ኢኮኖሚክስ እና ሰላም ናቸው።

በሰፊና ሁሴን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review