ከፒኤስጂ ጋር መጫወት ቀላል አይሆንም – አሰልጣኝ ኧርን ስሎት

You are currently viewing ከፒኤስጂ ጋር መጫወት ቀላል አይሆንም – አሰልጣኝ ኧርን ስሎት

AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም

ከአርሰናልም ሆነ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ትልቅ ጨዋታዎችን አድርገናል፤ ፒኤስጂ ግን ጥራት ያለዉ እና ሁሉ ነገሩ የተሟላ ቡድን ነዉ፤ ከእነሱ ጋር በተቃራኒዉ መጫወት ቀላል አይሆንም በማለት የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ኧርን ስሎት ከሻምፒየንስ ሊጉ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ በፊት ተናግረዋል፡፡

የአዉሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 5 ሰአት ላይ ተጠባቂዉ የሊቨርፑል እና የፒኤስጂ ጨዋታ አንፊልድ ላይ ይደረጋል ፡፡

ባለፈዉ ሳምንት ፓርክደስ ፕሪንስ ላይ በበረዉ ጨዋታ ሊቨርፑል በሀርቬ ኢሊዮት ግብ 1ለ0 አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡

በሊቨርፑል በኩል ኮዲ ጋክፖ ከጉዳቱ አገግሞ መመለሱ ለክለቡ መልካም ዜና ነዉ ተብሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ሁለቱን የጀርመን ክለቦች ባየርሊቨርኩሰን እና ባየር ሙኒክን በባይ አሬና የሚያገናኘዉ ጨዋታ ነዉ፡፡

በመጀመሪያዉ ጨዋታ ባየር ሙኒክ 3ለ0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ሩብ ፍፃሜዉን ለመቀላቀል የተሻለ እድልን ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ኢንተር ሚላን በተመሳሳይ ሰአት በጁሴፔ ሜኤዛ ፌይኖርድን ያስተናግዳል፡፡

ባለፈዉ ሳምንት ሆላንድ ላይ በማርከስ ቱራም እና ላዉታሮ ማርቲኔዝ ግቦች 2ለ0 አሸንፎ የተመለሰዉ ኢንተር ሚላን በዛሬዉ ጨዋታም የአሸናፊነት ቅድመ ግምትን አግኝቷል፡፡

በቅርቡ ባደረጋቸዉ 5 ጨዋታዎች ግብ ያላስተናገደዉ ኢንተር ሚላን በዛሬዉ ጨዋታም መረቡን ላለማስደፈር ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ ሊያደርግ ይችላል ተብሏል፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ደግሞ ባርሴሎና በሜዳዉ ቤኔፊካን ያስተናግዳል፡፡

የመጀመሪያዉን ጨዋታ በጎዶሎ ተጫዋች 1ለ0 አሸንፈዉ የተመለሱት ባርሳዎች ሩብ ፍፃሜዉን ለመቀላቀል ከቤኔፊካ ከባድ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡

በአልማዝ አዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review