የጉምሩክ ኮሚሽን ከመስከረም 26 ቀን እስከ ጥቅምት1/2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 131 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 23 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 155 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን ገልጿ፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ኮሚሽኑ አስታውቋ ል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻው የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪ ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ