ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

You are currently viewing ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ግምታቸው 160 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ የኮትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ-3 ኢት. 71945፣ ኮድ-3 ኢት. 14071፣ ኮድ-3 ኢት. 74192 እና ኮድ-3 ኢት. 74632 በሆኑ አራት ተሽከርካሪዎች ከ160 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ልባሽ እና አዳዲስ ልብሶች፣ ለምግብነት የሚያገለግሉ ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የቤት ዕቃዎች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ የወለል ምንጣፎች፣ የተለያዩ የሞባይል ቀፎዎች፣ ጫማዎች፣ መድሃኒቶች፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች፣ ሽቶዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደብተሮች፣ የዝናብ መከላከያ ሸራዎች፣ ሚስማሮች፣ የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖች፣ መነጽሮች፣ ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች እና የተለያዩ የውበት መጠበቂያ ክሬሞች በመጫን መነሻቸውን ሱማሌ ላንድ በማድረግ ወደ ድሬ ዳዋ ከተማ በመግባት ላይ ሳሉ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት ልዩ ስሙ አርሙ ካሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አባላት እና በጉሙሩክ ሰራተኞች የተቀናጀ ሥራ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ አንድ መቶ ስልሳ ሚሊየን አምስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር የሚገመቱ ሲሆን በጉሙሩክ ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርጫፍ ገቢ ተደርጎ በምርመራ እየተጣራ ይገኛል።

ህብረተሰቡ ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሚያደርሰውን ጉዳት በመገንዘብ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ላለው ትብብር ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረበ ይህንኑ ቀና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review