AMN-መስከረም 21/2017 ዓ.ም
በሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ መነሻቸውን በአዲስ አለም እና ሰጋሎ አካባቢ በማድረግ የህዝቡን ሠለም ሲያውኩ በነበሩ የፅንፈኛ በድኖች ላይ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
የሠላምን አማራጭ ወደ ጎን በመተው የዘረፋና የውንብድና ተግባር ሲፈፅሙ በነበሩ የፅንፈኛው አባላት ላይ ክፍለጦሩ በወሰደው ድንገተኛ እርምጃ 10 ሲደመሰሱ ሁለቱ ደግሞ መማረካቸውን ነው በቀጠናው ተልዕኮ በመፈፀም ላይ የሚገኘው ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ጃዋር ዴኮ የተናገሩት።
ለህዝባችን ሠላም ስንል ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት እንከፍላለን ያሉት ኮሎኔል ጃዋር ዴኮ ዘራፊውን ቡድን የገባበት ገብተን በመደምሰስ የቀጠናውን ሠላምና ፀጥታ እናረጋግጣለን ብለዋል።
አዛዡ አክለውም በወረዳው በተደረገ ድንገተኛ አሰሳ ለፅንፈኛው በተለያየ መንገድ ድጋፍ ሲያደጉ የነበሩ ሴሎች ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 115 ክላሽን ኮቭ ጠመንጃ፣15 ኋላቀር መሣሪያ ፣08 ሽጉጥ፣ 2 M14፣ 5 ሺህ 592 የክላሽ ጥይት፣ 150 የክላሽ ከዝና፣ 17የእጅ ቦምብ፣567 የመትረየስ ጥይት፣2 የመትረየስ ሸንሸል ፣77 የወገብ ትጥቅና 26 የፅንፈኛው አልባሳት እንዲሁም ድምፅ አልባ ስለት መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ጃዋር ዴኮ ተናግረዋል።
ህግ የማስከበር ተልዕኳችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አዛዡ ኮሎኔል ጃዋር ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት የሚያደርገውን ድጋፍና ትብብርም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አመልክቷል።