AMN-ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
የደቡብ ዕዝ ነበልባል ክፍለጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ምስራቅ አርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ ጃዊ ጭላሎ ቀበሌ ልዩ ስሙ ለመፍ በተባለ ቦታ ለይ የህዝብን ሰላም በመንሳት ላይ በነበረው ኦነግ ሸኔ ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ለታ አንበሴ ተናግረዋል።
ክፍለጦሩ የተሰጠውን ሃገራዊ ተልእኮ በብቃት እየተወጣ መሆኑን ገልፀው፤ በአሽባሪው ሽኔ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እጅግ ስኬታማ መሆኑንም ገልፀዋል።
አሸባሪው የሚንቀሳቀስባቸውን ቀጠናዎች በመለየትና በቂ የሆነ መረጃዎችን በማሰባሰብ እንዲሁም የአካባቢው የፀጥታ ሃይል እና ማህበረሰቡ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን መውጫ መግቢያ በማሳጣት አሸባሪው የሸኔ ቡድን እንዲፈረካከስና እንዲደመሰስ ተደርጓልም ነው ያሉት።
ከተደመሰሰው ውጪ ለሠራዊቱ እጃቸውን የሰጡ የሽብር ቡድኑ አባላት 28 ሲሆኑ ክላሽ 7 ፣ኋላቀር መሳሪያ 12፣ የክላሽ ጥይት 667 በመማረክ የሸኔን ህልም ማክሸፍ መቻሉንም አሥረድተዋል።
አሸባሪው ሃይል መንግስት ያቀረበለትን የሰላም ጥሪ አልቀበልም በማለት ህብረተሰቡን መዝረፍ ፣ መግደል፣ ማፈናቀሉን በመቀጠሉ በሚገባው ቋንቋ በማናገር ልክ የማስገባት እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።